ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጅማ ዞን፣ በሻሻ ከተማ ያስገነቡትን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው ቀን አስመርቀዋል፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት እየተገበራቸው ካሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ውስጥ ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ አን መሆኑ ተመላክቷል።
በዚህም ላለፉት 5 ዓመታት በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች በአጠቃላይ 34 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ ከ40,000 በላይ ለሆኑ ተማሪዎች ትምህርት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ ይህንኑ ተግባር አጠናክሮ በመቀጠል ዛሬ 35ኛውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስመርቋል።
ትምህርት ቤቶች በአቅራቢያ በማይገኙባቸው ቦታዎች የተገነቡት በትምህርት ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት፣ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት፣ ትውልድን በትምህርት ለማነጽና የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
መረጃው የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ነው
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












