ባሳለፍነው የውድድር አመት አጋማሽ ኤቨርተንን በድጋሚ ማሰልጠን የጀመሩት ሞይስ፣ክለቡ በዝውውር ገበያው በንቃት አለመሳተፉ እንዳበሳጫቸው ተናግረዋል።
“የዝውውር መስኮቱ ሊጠናቀቅ ጥቂጥ ጊዜ በቀረበት ሰዓት ወሳኝ የሚባል ትልቅ ተጫዋች አላስፈረምንም ያሉት” ሞይስ “በፍጥነት ተጫዋቾች ካላመጣን በቀጣይ የውድድር አመት ልንቸገር እንችላለን ብለዋል።
ኤቨርተን በትላንትናው ዕለት ይፋ ያደረገውን የአዳም አዙኑን ዝውውር በተመለከተም ‘’በዋናው ቡድን መሰለፍ አለመሰለፉ የሚያስተማምን አይደለም በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የመርሲሳይዱ ክለብ የቡድን ስብስቡ በእጅጉ እየሳሳ የሚገኝ ሲሆን፣ተተኪ የሚሆኑ ተጫዋቾች እስካሁን አለመምጣታቸው ለደጋፊዎች አሳሳቢ ሆኗል። የደጋፊዎችን ስጋት የሚጋሩት አሰልጣኙም ክለቡ አዳዲስ በቡድኑ ውስጥ ለውጥ የሚፈጥሩ ተጫዋቾችን እንዲያስፈርም ግፊት አድርገዋል።
ኤቨርተን በዝውውር ገበያው ካይል ወከርን፣ጃክ ግሪሊሽን ጨምሮ ከበርካታ ተጫዋቾች ጋር ስሙ ቢያያዝም አንዱንም የራሱ ማድረግ ተስኖታል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












