ቪላ በዝውውር መስኮቱ በበርካታ ክለቦች እየተፈለገ የሚገኘውን የፊት መስመር ተጫዋቹን በክለቡ ለማቆየት በውይይት ለይ እንደሚገኝ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
እንግሊዛዊው ሞርጋን ሮጀርስ ወደ ቼልሲ በያዝነው ክረምት ሊጓዝ ይችላል ቢባልም፤ በቪላ ፓርክ የሚቆይበት ዕድል ሰፊ መሆኑ ተነግሯል። አስቶን ቪላ ተጫዋቹን ባሳለፍነው አመት አዲስ የአምስት አመት ውል ቢያስፈርመውም፣አሁንም የሚከፈለውን ደመወዝ በመጨመር ውሉን ሊያድስ በዝግጅት ላይ ነው ተብሏል።
ሮጀርስ ባሳለፍነው የውድድር አመት በአስቶን ቪላ ድንቅ የተባለ አቋም ማሳየት የቻለ ሲሆን፤ በአሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ጥሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን መጫወት ችሏል። ይህንን አስደናቂ አቋሙን ተከትሎ የልጅነት ክለቡ ማንችስተር ሲቲ፣ ቼልሲ፣ ቶተንሃም እና ማንችስተር ዩናይትድ የተጫዋቹን ግልጋሎት የፈለጉ ቡድኖች ናቸው።
አስቶን ቪላ የእነዚህን ክለቦች ፍላጎት ለመግታት የረጅም ጊዜ ውል ያስፈርመዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












