ለሰሜን ለንደኑ አርሰናል ለመፈረም ተቃርቦ የነበረው እንግሊዛዊው አጥቂ የመርሲሳይዱን ክለብ መምረጡ ታውቋል።
በእንግሊዝ የሊግ እርከን ሶስተኛ በሆነው ሊግ 1 በሚወዳደረው ሳልፎርድ ሲቲ የሚጫወተው ራይት፣ ክለቡ ሳልፎርድ እና አርሰናል ስምምነት ላይ ቢደርሱም፣ተጫዋቹ ከመድፈኞቹ ጋር በግል ጉዳዮች ላይ መስማማት አልቻለም ተብሏል።
አርሰናል ለሳልፎርድ ሲቲ ያቀረበው 200ሺ ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ተቀባይነት ማግኘት ችሎ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ተጫዋቹ የቀዮቹን የታዳጊ ቡድን ለመቀልቀል ተስማምቷል። እምቅ ችሎታ አለው የተባለው የ17 አመቱ ራይት ለሳልፎርድ የመጀመሪያውን ጨዋታ ያደረገው ከማንችስተር ሲቲ ጋር በነበረ የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ ላይ ነበር።
ታዳጊው ተጫዋች በቀጣዮቹ ቀናት የህክምና ሂደቱን አጠናቆ በሮብ ፔጅ የሚሰለጥነውን ከ21 አመት በታች የሊቨርፑል ቡድን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












