በሩሲያ 8 ነጥብ 8 መጠን ያለው አደገኛ ርዕደ መሬት መከሰቱ ፓስፊክ ውቅያኖስ በከባዱ ተናጠ።
የሩሲያ ሩቅ ምስራቅ ካምቻትካ ልሳነ ምድር ርዕደ መሬትን ተከትሎ ክፉኛ አካባቢው በማዕበል መመታቱም ታውቋል። ከ3 እስከ 4 ሜትር ከፍታ ያለው ማዕበል (ሱናሜ) በአካባቢው ላይ መመዘገቡ የተነገረ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ሞገድ በሰሜናዊ ጃፓን ሆካኢዶ ከተማ በ30 ሴንቲ ሜትር ከፍታ ማዕበል አካባቢው ታውኳል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት በአላስካ እና ሃዋኢ ግዛቶች ዜጎች የሱናሚ ማዕበል ተጠንቀቅ ውስጥ እንዲሆኑም አዘዋል። የርዕደ መሬት ባለሙያዎች (ሴስሞሎጂስትስ) የመሬት መንቀጥቀጡ እና ማዕበሉ በ1940ዎቹ ከተከሰተው አስፈሪ አደጋ ጋር አመሳስለውታል።
ዛሬ በሩሲያ የተከሰተው ርዕደ መሬት በታሪክ ስድሰተኛው አስከፊ “የመሬት መንቀጥቀጥ ነው” ብለዋል ባለሙያዎች። በ2010 በቺሊ እና በ1890ዎቹ በኢኳዶር እንደተመዘገበው ዓይነት የከፋው እንደማለት ነው።
በሌላ በኩል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የማዕበል አደጋ ማስጠንቀቂያውን ለሃዋኢ እና አላስካ ግዛቶቻቸው ሰተዋል። ህዝቡም እንዲረጋጋ ጠይቀዋል ትራምፕ። ደህንነታችሁን እየጠበቃችሁ በርትታችሁ ቆዩን ብለዋል።
በጃፓን፣ አሜሪካ እና ሩሲያ ዜጎች ከባድ የባህር ሞገድ እና ማዕበል ስጋት ውስጥ ናቸውም በሚልም የአደጋው ክፋት ተገልጿል።
ዘገባው የ ዘ ዋሽንግተን ፖስት እና ሲ ኤን ኤን ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












