አውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ የ15 በመቶ የታሪፍ ንግድ ስምምነት ላይ ደረሱ።
ሁለቱ ግዙፍ የኢኮኖሚ አጋሮች ለወራት በቀረጥ ሳቢያ ሲከራከሩ እንዲሁም ልዩነታቸውን ለማጥበብ ሲሞክሩ ቆይተዋል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ዲዬር ሊዬን በስኮትላንድ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
30 በመቶ የነበረውን የአሜሪካ ከአውሮፓ ህብረት የሚገቡ ምርቶች ላይ የሚጣል የገቢ ታክስን በግማሽ ዝቅ ያደረገ ነው። ትራምፕ ባለ 27 ዓባላቱ አውሮፓ ህብረት ለአሜሪካ ላኪዎች ገበያውን እንዲከፍትም አሳስበዋል።
በተወሰኑ ምርቶች ላይም ምንም ቀረጥ አገራቱ እንዳይጥሉ አሳስበዋል። ኡርሱላ ቮን ዲዬር ሊዬንም ስምምነቱን ያደነቁ ሲሆን፣ በሁለቱም ወገኖች በኩል የገበያያ መረጋጋትን ይፍጥራል ብለውታል።
በአሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት መካከል ያለው የምርት ንግድ ልውውጥ በ2024 976 ቢሊዬን ዶላር ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል። አሜሪካ 606 ቢሊዬን ዶላር የሚገመት ምርት ከአውሮፓ ህብረት ስታስገባ 370 ቢሊዬን ዶላር ምርት ደግሞ ወደ ህብረቱ ልካለች።
ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ እንዳስነበበው
በ- ቢኒያም ካሴ












