አምስተኛ ቀኑን በያዘው የድንበር ላይ ግጭትን ለመፍታት በታይላንድ እና በካምቦዲያ መሪዎች መካከል የተኩስ አቁም ውይይት በማሌዥያ መካሄድ ተጀምሯል።
በሁለቱ የደቡብ ምስራቅ እስያ ተፋላሚ ሀገራት መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ በትንሹ የ35 ሰዎችን ህይወት የተቀጠፈ ሲሆን ከ270,000 በላይ የሚሆኑ ዜጎችን ያፈነቀለን ጦርነት ነው። ይሄን ውጊያ ለማስቆም በማሌዢያ አስተናጋጅነት ውይይት እየተደረገ ነው።
የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም እንደተናገሩት፣ የውይይቱ አላማ አፋጣኝ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ ነው፡፡ በስብሰባው ላይ የአሜሪካ እና የቻይና አምባሳደሮችም መገኘታቸውን አክለውም ገልጸዋል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው
በ – ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












