በሰሜናዊ ቻይና ሄቤይ ግዛት ባልተለመደ መልኩ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክኒያት በተቀሰቀሰው የመሬት መንሸራተት አራት ሰዎች ሲሞቱ ስምንት ሰዎች ደግሞ ደብዛቸው ጠፍቷል።
የሰሜናዊ ቻይና ግዛት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከባድ የሆነ የዝናብ መጠን እያስተናገደች ሲሆን፤ ቤጂንግን ጨምሮ ብዙ ህዝብ የሚኖርባቸውን ከተሞችም ለጎርፍ አደጋ አጋልጧቸዋል።
በተመሳሳይ በቤጂንግ ማይዩን ከተማ ዳርቻ ላይ በጣለው ከባድ ዝናብ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ በማስከተሉ በርካታ መንደሮች ወድመዋል፡፡ የቻይና ባለስልጣናትም ከ4,400 በላይ ሰዎችን ወደ ሌላ ቦታ ማዘዋወራቸው ተገልጿል፡፡
የአየር ንብረት ባለሞያዎች እንደገለጹትም ይህ ከባድ ዝናብ በሚቀጥሉት ሶስት ቀናትም ቀጣይነት እንዳለው የገለጹ ሲሆን የቻይና የውሃ ሀብት ሚኒስቴርም በ11 ክልሎች ላይ የጎርፍ አደጋ ስጋት በመኖሩ ምክንያት ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












