ወደ አሜሪካ አቅንቶ ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅቱን እያደረገ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ 9 አባላት ቪዛ መከልከላቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።
የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ዛሬ ጠዋት የአሜሪካ ኤንባሲ በር ላይ የቀጠሮ ሰዓታቸውን በመጠባበቅ መግባት መግባት ቢችሉም ወደ አሜሪካ የሚያስገባቸውን ፈቃድ ተከልክለዋል። ቪዛ ከተከለከሉት ውስጥ ሰባት ተጫዋቾች እና ሁለት የአሰልጣኞች ቡድን አባላት እንደሚገኙበት ታውቋል።
ከእነዚም ውስጥ ከተጫዋች ወገኔ ገዛኸኝ ፣ መሐመድ አበራ ፣ ያሬድ ካሳየ ፣ቢኒያም ገነቱ፣ አህመድ ሁሴን ፣ ቢንያም አይተን፣ በረከት ደስታ እና አብዱልከሪም ወርቁ ይገኙበታል ተብሏል። የብሔራዊ ቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ ተመስገን ዳናም ቪዛ ከተከለከሉት መካከል እንደሚገኙ ተረጋግጧል።
አሁን ባለው ሁኔታ ለወዳጅነት ጨዋታው ጥሪ ከተደረገላቸው 23 ተጫዋቾች መካከል ወደ ከቡድኑ ጋር የሚቆዩት 15 ተጫዋቾች መሆናቸው ታውቋል። ብሔራዊ ቡድኑ ልምምዱን አጠናቆ የፊታችን ማክሰኞ ወደ አሜሪካ የሚጓዝ ሲሆን፣ ሐምሌ 26 ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።
ቪዛ ባላገኙት ተጫዋቾች ምትክ ሌሎች አማራጮች ይኖራሉ ወይስን 15 ተጫዋቾች ብቻ ይጓዛሉ የሚለው በቀጣይ የሚታይ ጉዳይ ይሆናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












