የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባዔውን በጅግጅጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አያን አብዲ ጉባዔውን ያስጀመሩ ሲሆን የጉባኤውን አጀንዳዎች ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡ በዚህም ምክር ቤቱ በጉባዔው የምክር ቤቱ 8ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባኤ ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እንዲሁም የክልሉ መንግሥት የ2017 የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርት ላይ እና የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ ከተያዙት አጀንዳዎች ዋናዎቹ መሆኑን አንስተዋል።
የክልሉ ፍትህ ቢሮ የ2017 እቅድ ሪፖርት፣ የክልሉ ኦዲት ቢሮ የ2017 እቅድ ሪፖርት እንዲሁም አዋጆችና የ2018 በጀት ላይ መክሮ እንደሚያጸድቅም አብራርተዋል። አፈ ጉባዔዋ ምክር ቤቱ የክትትል እና ቁጥጥር እንዲሁም የህዝብ ውክልና ስራ ለመስራት ሰፊ ርብርብ በማድረግ አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉንም ተናግረዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












