Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

“የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየሰራን የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤን ለማስተናገድ ተዘጋጅተናል” የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

"የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየሰራን የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤን ለማስተናገድ ተዘጋጅተናል" የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

July 26, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

July 26, 2025

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በአዲስ አበባ የሚካሔደውን 2ኛውን የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየሰራን የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤን ለማስተናገድ ተዘጋጀተናል!

ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በጀመረቻቸው ጥረቶች በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል፤ ለላቀ ስኬትም ጥረቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

በዚህ ወሳኝ ወቅት ኢትዮጵያ ከጣልያን መንግሥት እና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በመቀናጀት 2ኛውን የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች።ይህም በኹለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ግንኙነቶች ውስጥ ኢትዮጵያ እየተጫወተች ያለውን ሚና የሚያጎላ፣ በሥርዓተ ምግብ ዙሪያ የጀመረቻቸውን ስኬታማ ተግባራት የሚያበረታታ ነው።

ከዐራት ዓመታት በፊት በመጀመሪያው የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤ ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎች ኢትዮጵያ በምታስተናግደው መድረክ ይገመገማል፤ ቀጣይ አቅጣጫዎችም ይቀመጣሉ። ኢትዮጵያ በምታስተናግደው ጉባኤ ርኃብን ስለማስወገድ እና ምግብ ዋስትና፣ ስለአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች ምክክር ይደረጋል፤ ቀጣይ መወሰድ የሚገባቸው ርምጃዎችም ይመላከታሉ።

ኢትዮጵያ ጉባኤውን የምታስተናግደው ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን በማስመዝገብ የማንሰራራት ጉዞን በጀመረችበት ወቅት ነው። ለጉባኤው በተሞክሮነት የምታካፍላቸው በርካታ ስኬቶችም አላት። በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በአረንጓዴ ዐሻራ ስኬታማ ድሎችን አስመዝግባለች።

በአየር ንብረት ለውጥ ረገድም ባለፉት በጣት የሚቆጠሩ ዓመታት ከ40 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ለዓለም አብነት ናት። ጉባኤው በሚካሄድበት በዚህ ክረምትም 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል እየተጋች ነው። የሚተከሉት ችግኞች የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ከማስቻላቸውም በላይ የምግብ ዋስትናን እና ሥርዐተ ምግብን ለማሻሻል ሚና ያላቸው ናቸው።

የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤን እንድታስተናግድ ለኢትዮጵያ ዕድል መሰጠቱም ይህንን ጅምር ዕውቅና የሚሰጥ ነው። ኢትዮጵያ ባለብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ እየገነባች እና ኹለንተናዊ ስኬት እያስመዘገበች ባለችበት በዚህ ወቅት ከሐምሌ 20-22/2017 ዓ.ም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ሥርዐት ጉባኤን በአዲስ አበባ ታስተናግዳለች።

በጉባኤው የሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ሳይንቲስቶች፣ የምግብ አምራቾች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ የሴቶች ድርጅቶች፣ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ይሳተፋሉ።

ኢትዮጵያም የመዲናዋን ገጽታ በእጅጉ ለውጣ እንግዶችን በላቀ ዝግጅት ለመቀበል ተሰናድታለች። በርካታ ስኬቶቿንም በልምድነት ለማካፈል ተዘጋጅታለች። የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ለዘመናት ያስቀጠሉትን ለኹለትዮሽና ባለብዝኃ ወገን ግንኙነት ትኩረት የመስጠት ልምድ ተጠቅመው ጉባኤውን በላቀ ስኬት ለማስተናገድ በቂ ቅድመ ዝግጅት አድርገዋል።

የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Source: @NBCEthiopia
Via: NBC Ethiopia
Tags: chinaEthiopiaFacebookhealthiranMetaRussiaRussia Ukraine warsporttrump
ShareTweetShare
Previous Post

ሀሰተኛ የባቡር ትራንስፖርት ትኬት በማዘጋጀት ሲሸጥ የነበረ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለ

Next Post

ራያ ምን እየተከናወነ ነው? ከኋላ ማን አለ?

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ራያ ምን እየተከናወነ ነው? ከኋላ ማን አለ?

ራያ ምን እየተከናወነ ነው? ከኋላ ማን አለ?

የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እስከመገንጠል

የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እስከመገንጠል

በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሃ ግብር

በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሃ ግብር

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?