የፖርቱጋሉ ክለብ የቼልሲውን የክንፍ መስመር አጥቂ የግሉ ለማድረግ ከቼልሲ ጋር በመነጋገር ላይ መሆኑን ታማኝ ምንጮች ዘግበዋል።
ጆዋው ፊሊክስ የምዕራብ ለንደኑ ቼልሲ በያዝነው የዝውውር ገበያ መልቀቅ ከሚፈልጋቸው ተጫዋቾች ዋነኛው ሲሆን፣ከውሰት ውል ይልቅ በቋሚነት መሸጥ ይፈልጋሉ ተብሏል።
የ25 አመቱ ፖርቱጋላዊ ያሳለፍነውን የውድድር አመት አጋማሽ በጣሊያኑ ኤሲ ሚላን በውሰት ማሳለፉ ይታወሳል፣ሚላን ተጫዋቹን በቋሚነት የመውሰድ ዕድል ቢሰጠውም ፈቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ ፊሊክስ ወደ እንግሊዝ ተመልሷል።
ቼልሲ ጆአው ፊሊክስ በሚጫወትበት ስፍራ በርካታ አማራጮቾች ያሉት ሲሆን፣በተመሳሳይ ቦታው ላይ ሊጠቀምበት በማሰብ ዣቪ ሲሞንስን ከአርቢ ላይብዚሽ ለማስፈረም ተቃርቧል። ፊሊክስ ከአመታት በፊት የባላንዶር ተስፋ ያለው ታዳጊ ነው በሚል በ120 ሚሊዮን ዩሮ አትሌቲኮ ማድሪድን ቢቀላቀልም ሳይሳካላት ቀርቷል።
ቼልሲ ከአትሌቲኮ ተጫዋቹን በቅድሚያ በውሰት በኋላም በቋሚ ቢያስፈርመውም በአሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ የቡድን ስብስብ አፈላጊ ሊሆን አልቻለም።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












