በታይላንድ ራዮንግ ግዛት የሚኖር አንድ ግለሰብ አልኮል በመጠጣት ብቻ ከአንድ ወር በላይ ከቆየ በኋላ ከመቶ በሚበልጡ ባዶ የቢራ ጠርሙሶች ተከቦ ህይወቱ አልፎል።
የነፍስ አድን ሰራተኞች ራዮንግ ግዛት ወደ ሚገኝ አንድ ቤት የተጠሩ ሲሆን ከቦታው ሲደርሱም ግለሰቡ ራሱን ስቶ ነበር፡፡ ሰራተኞቹም እንደገለጹት በመኝታ ቤቱ ወለል ላይ በጥሩ ሁኔታ ተስተካክለው የተቀመጡ የቢራ ጠርሙሶችን አግኝተዋል፡፡
የ44 አመቱ ታዌሳክ ናምዎንግሳ ከአንድ ወር በላይ ቢራ ብቻ ይጠጣ እንደነበር እንዲሁም ለወር ያክል ምንም ዓይነት ምግብ እንዳልተመገበ ተገልጿል፡፡
የናምዎንግሳ ልጅ ከትምህርት ቤት ሲመለስ በየቀኑ ለአባቱ ትኩስ ምግብ እንደሚያበስል ለፖሊስ ተናግሮል፤ ነገር ግን አባቱ ምንም ነገር ለመብላት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ከአንድ ወር በላይ በቢራ ብቻ እየኖረ ነበር።
የጤና ባለሙያዎች ቢራ በመጠኑ መጠጣት እንዳለበት ያስጠነቅቃሉ። ቢራ አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች የሉትም እንዲሁም ምግብንም ሊተካ አይችልም፡፡
በ- ሔርሜላ ተመስገን












