የምዕራብ ለንደኑ ክለብ በያዝነው የዝውውር መስኮት በንቃት እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን፣በክንፍ መስመር ላይ ቫቪ ሶሞንስን የራሳቸው ለማድረግ ተቃርበዋል።
የ22 አመቱ ሲሞንስ ቼልሲን ለመቀላቀል በግል ጉዳዮች ላይ ከስምምነት መድረሱን ታማኝ መረጃ የሚያወጡ መገናኛ ብዙሃን ዘግበውታል። በሁለቱ ክለቦች መካከል ውይይት እየተካሄደ ሲሆን፣የሆላንዳዊው ተጫዋች መዳረሻ ስታንፎርድ ግሪጅ መስሏል።
ቫቪ ሲሞንስ ለአርቢ ላይብዚሽ ያሳለፍነውን የውድድር አመት አጋማሽ በውሰት ውል ከፒኤስጂ የተጫወተ ሲሆን፣የጀርመኑ ክለብ ዝውውሩን በ50 ሚሊዮን ፓውንድ ቋሚ ያደረገው በጥር ወር ላይ ነበር።
ቼልሲ በስፍራው ላይ ያሉትን ንኩንኩ፣ጆአው ፍሊክስ እና ስተርሊንግን በመልቀቅ ቫቪ ሲሞንስን የቀጣይ አመት አሰላለፍ ላይ ማካተት ይፈልጋል ተብሏል። የሰሜን ለንደኑ አርሰናልም የተጫዋቹ ፈላጊ ነው ሲባል ቢቆይም፣ቼልሲ ዝውውሩን ለመፈጸም የተሻለ መጓዝ ችሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












