በዋሽንግተን ኦፕን በተደረገ የጥምር ሴቶች የቴኒስ ጨዋታ ቬኑስ ዊሊያምስ እና ሃይሊ ባብቲስት ተጋጣሚዎቻቸው ኢውጊን ቦካርድ እና ክለርቪ ንጎኒ ላይ ድል ተጎናጽፈዋል።
ዊሊያምስ እና ባብቲስት ተጋጣሚዎቻቸው ላይ የጨዋታ የበላይነት በመውሰድ 6-3 እና 6-1 በሆነ አጠቃላይ ውጤት አሸንፈዋል። ቬኑስ ዊሊያምስ ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ ወደ ሜዳ የተመለሰች ሲሆን፤ ከቆይታ በኋላ ድል ማድረጓ አድናቆት አስገኝቶላታል።
የ45 አመቷ ዊሊያምስ በ22 አመት በዕድሜ የምትበልጣት ተጣማሪዋን ባብቲስትን ለውጤቱ መገኘት ከፍተኛ አስተዋጾ አድርጋለች በሚል አስተያየቷን ሰጥታለች። የ7 ጊዜ የግራንድ ስላም አሸናፊዋ ዊሊያምስ ዛሬ ምሽት አሜሪካዊቷን ፔይተን ስቲርንስን የምትገጥም ይሆናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












