እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ የሚቀጥልውን የውድድር አመት በውሰት ውል ለማሳለፍ ወደ ባርሴሎና በመጓዙ ይታወሳል።
ባርሴሎና ባለፉት አመታት በገጠመው የፋይናንስ ቀውስ መነሻነት የሚያስፈርማቸውን ተጫዋቾች በስፔን ላሊጋ ለማስመዝገብ እየተቸገረ ይገኛል። አምና አማካኙን ዳኒ ኦልሞን ለማስመዝገብ እንደገጠማቸው ፈተና፤ አሁን ላይ ደግሞ ማርከስ ራሽፎርድ ላይ በተመሳሳይ ሊቸገሩ እንደሚችል ዘ ሰን ዘግቧል።
ባርሳ የተጫዋቹን 12 ሚሊዮን ፓውንድ አመታዊ ደመወዝ ለመክፈል የተስማማ ሲሆን፤ ለአንድ አመት በውሰት ውል ከተጠቀሙበት በኋላ በ36 ሚሊዮን ፓውንድ ዝውውሩን ቋሚ የማድረግ አማራጭ ተካቶላቸዋል።
የ27 አመቱ ማርከስ ራሽፎርድ በ2026 አለም ዋንጫ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የመጫወት ተስፋው ለባርሴሎና መሰለፍ ካልቻለ አጣብቂኝ ውስጥ ይገባል። ባርሳ በያዝነው የክረምት የዝውውር ገበያ ከኤስፓኞል ያስፈረሙትን ግብ ጠባቂ ዮሃን ጋርሺያንም በስፔን ላሊጋ እስካሁን ማስመዝገብ አልቻሉም።
የላሊጋው ፕሬዚዳንት ከወራት በፊት በሰጡት አስተያየት ባርሴሎና ተጫዋች አስፈረመ ማለት በሜዳ ላይ እንደሚጠቀምባቸው ማረጋገጫ አይሆንም በማለት መናገራቸው ይታወሳል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












