ኢራን “በእስራኤል ጥቃት የወደሙብኝ የዓየር መከላከያ ሰርዓቶቼ ተተክተዋል” አለች።
የኢራን ጦር ቁልፍ ባልደረባ ማህሙድ ሙሳቪ ናቸው ይህን ያሉት። “የተወሰኑ የአየር መከላከያ ስርዓቶች ወድመውብን ነበር ፣ ይህን የምንደብቀው ነገር አይደለም። ነገር ግን ባልደረቦቻችን ተክተዋቸዋል” ብለዋል።
የአገር ውስጥ ሀብት በመጠቀም እና ስርዓቶቹን ዳግም በማስተካከል የወደሙትን የመተካት ስራ መከናወኑንም የሚጠቁም መረጃ ከቴህራን በኩል ይፋ ተደርጓል። በተስማሚ አካባቢ ላይ ተደብቀው የተቀመጡ እንደነበሩም ሙሳቪ አሳውቀዋል።
እስራኤልና ኢራን ለ12 ቀናት የአየር ለአየር ውጊያ ሲያደርጉ በርካታ ውድመቶችን እርስ በርስ አስከትለዋል። አገራቱ ውጥረታቸውን በአሜሪካ አሽማጋይነት ለጊዜው ማቆማቸው ቢታወቅም አንድ ቀን ዳግም ወደ ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ የሚል ስጋትም አለ።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው።
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












