የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን “የሞስኮ ሉዓላዊ ስጋት ነው” ያሉትን ሀሳብ ይፋ አደረጉ።
ከልክ ያለፈ የውጭ አገራት የቴክኖሎጂ ምርት ላይ ጥገኛ መሆን፣ የነዳጅና ጋዝ ገቢ ላይ ትኩረት ማድረግ የሩሲያ ሉዓላዊነት ላይ ስጋት ይጋርጣሉ ብለዋል ፑቲን። ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ በነዳጅ እና ጋዝ ብቻ የተንጠለጠለ ገቢ ላይ ትኩረት ካደረገች ሉዓላዊነታችን ይጣሳል በሚል አስጠንቅቀዋል።
የአገር ውስጥ ምርትን ችላ ማለትም ለሩሲያ አደጋ ይሆናል የሚል ስጋታቸውን አስቀምጠዋል ። ለበርካታ አስርት ዓመታት የተሽከርካሪ ምርቶችን በአገር ቤት እንዲመረቱ ስለተደረጉ ጥረቶች ያስገነዘቡት ፑቲን፣ ይህን ያደረግነው የሩሲያን ኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ለመታደግ እንዲሁም ራሱን የቻለ ለማድረግ ነው በሚል አረጋግጠዋል።
ፕሬዚዳንቱ በ1990ዎቹ የመንግስታቸው አብዛኞቹ ዓባላት የመኪና ፋብሪካዎችን “በመተው” ከውጭ አገራት በሚገቡ ምርቶች ላይ እናተኩር ብለው ነበር በሚል ያስታውሳሉ። በወቅቱም ፑቲን ተቃውመውት እንደነበር ይፋ አድርገዋል።
“ስለ በቴክኖሎጂ ራስን መቻል ማውራት አለብን፣ በነዳጅና ጋዝ ገቢ ሁሉን ነገር ከገዛን ፈተና ነው፣ ምዕራቡ ከነዳጅ እና ከጋዝ እያስወጣን ነው፣ ከዛም ሩሲያ ተወዳደሪ የመሆን አቅም ታጣለች፤ ሉዓላዊነትም እንደዛው።” በሚል ፑቲን ህዝባቸውን አስጠንቅዋል።
ዘገባው የአር ቲ ነው።
በ-ቢኒያም ካሴ












