የአርሰናሉ ተከላካይ ጋብሬል ማግሃሌሽ አዲሱ የውድድር አመት ከዚህ ቀደሙ የተለየ ይሆናል ሲል ተናገረ።
ለሶስት የውድድር አመት ለዋንጫ መፎካከር የቻለው አርሰናል በአዲሱ የውድድር አመት ዋንጫው ለማሳከት ይሰራል ሲል ብራዚላዊው ተከላካይ ለቢቢሲ ተናግሯል። “ያለፉትን አመታት ዋንጫውን ለማሳካት የተቻለንን አድርገናል” ያለው ማግሃሌሽ “ጥቂት እድለ ቢስ የነበርንባቸው አጋጣሚዎች ከዋንጫው አሰናክኖላን” ብሏል።
ማግሃሌሽ”ያለፉትን ጊዜ እያነሱ ሰበብ መደርደር አያስፈልግም ያለ ሲሆን አሰልጣኛችን የሚነግረንን በመቀበል ካለፉት ጊዜ በተሻለ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማሸነፍ ተዘጋጅተናል” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
በያዝነው የዝውውር ገበያ መድፈኞቹን ስለተቀላቀሉ አዳዲስ ተጫዋቾች በሚመለከትም ” ቡድናችንን የበለጠ ያጠናክሩታል፣በተጋጣሚዎቻችን እንዳንገመት ያደርገናል” በማለት ክለቡ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታን ለማገዝ የሚያደርገውን ጥረት አድንቋል።
የሰሜን ለንደኑ አርሰናል እስካሁን ባለው በተከላካይ፣በአማካኝ እና የክንፍ አጥቂ ክሪስቲያን ኖርጋርድን፣ኖኒ ማድዌኬን እና ክሪስቲያን ሞስኬራን ማስፈረም ችሏል። የዝውውሩ ሂደት አሰልቺ ቢሆንም በቀጣይ ጊዜያት በአንገብጋቢነት ተጫዋች በሚያስፈልገው የአጥቂ መስመር ቪክቶር ዮኬሬሽን ያስፈርማል ተብሎ ይጠበቃል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












