የክንፍ መስመር አጥቂውን አንቶኒ ኤላንጋን ለኒውካስትል ዩናይትድ የሸጠው ኖቲንሃም ፎረስት ተተኪውን ዳን ንዶዬን ለማፈረም ከቦሎኛ ተስማምቷል።
ዳን ንዶዬ የጣሊያኑን ክለብ ቦሎኛን የተቀላቀለው በ2023 ሲሆን፣ለክለቡ 97 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 12 ጎሎችን ሲያስቆጥር ፣15 ወደ ግብ የተለወጡ ኳሶች አመቻችቶ መቀበል ችሏል።
ፎረስት በስፍራው ላይ አስቀድሞ ለማስፈረም የፈለገው የፒኤስቪውን ዮሃን ባካዮኮን የነበረ ቢሆንም፣የተጫዋቹ ፍላጎት የጀርመኑን አርቢ ላይብዚሽን መቀላቀል ሆኗል።
የ24 አመቱ ዳን ንዶዬ በሚቀጥሉት ቀናት የህክምና ሂደቱን ለማጠናቀቅ ወደ ሲቲ ግራውንድ ይጓዛል የተባለ ሲሆን፣ፎረስት ለዝውውሩ እስከ 40 ሚሊዮን ፓውንድ ይከፍላል ተብሏል።
ስዊዘርላንዳዊው ተጫዋች በቀኝም በግራም መስመር የመጫወት ክህሎት መያዙ ለአሰልጣኝ ኑኖ ስፕሪቶ ሳንቶ ቡድን ጥንካሬ ይሰጣል ተብሎ ይገመታል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












