የሶሪያ ቤዱዊን ተዋጊዎች ወደ ጦር ሜዳ ሊመለሱ እንደሚችሉ አስታወቁ።
ድሩዞች እና ቤዱዌኖች ለአንድ ሳምንት በሱዌይዳ ግዛት ውስጥ ተዋግተዋል። የአል ሻርዓ’ መንግስት ባደረገው የተኩስ አቁም ጥሪ ለጊዜው ተፋላሚዎቹ ከስምምነት ቢደርሱም አስቸጋሪ ሀሳቦች አሁን ላይ እየተደመጡ ይገኛል።
አሜሪካም ተኩስ አቁሙ እሁድ አመሻሽ ላይ ገቢራዊ መደረጉንም አሳውቃለች። የቤዱዊን ተዋጊዎች በሱዌይዳ ከተማ አቅራቢያ ላይ ሰፍረው ወደ ጦርነቱ ሊመለሱ እንደሚችሉ በቢቢሲ በኩል አሳስበዋል።
ዳግም ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ የሶሪያ ፖለቲካ ከትላንቱ ዛሬ አደጋው የከፋ ይሆንበታልም ተብሏል። በውጥረቱ ላይ እስራኤል የድሩዞች ደጋፊ እንደሆነች መረጋገጡም ተጨማሪ ስጋትንም የፈጠረ አድርጎታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከድሩዝ ወንድሞቻችን ጋር አብረን እንቆማለን ማለታችውም አይዘነጋም።
ቢቢሲ እንደጻፈው።
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












