የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት ከ5.2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የገነባቸዉን 150 የትምህርት ቤት ፕሮጀክቶችን አስመርቆ ለአገልግልሎት ክፍት አደረገ።
ፕሮጀክቶቹ በጥራትና ደረጃቸዉን ጠብቀዉ የተሰሩ 14 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች፣ 64 ነባር ትምህርት ቤቶች ላይ በማስፋፋያ ስራ የተገነቡ 1,655 የመማሪያ ክፍሎች፣ የአይሲቲ ክፍሎች፣ ቤተ ሙከራዎች፣ የመመገቢያ አዳራሾች፣ ቤተ መፅሀፍቶች፣ የስፖርት ሜዳዎች፣ ጊቢዎችን ፅዱና ዉብ የማድረግ ስራ፣ የመጸዳጃ ቤቶች እና የውሃ አገልግሎትን ጨምሮ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እና መምህራን ምቹ የማድረግ ስራዎችን ያካተቱ ናቸው።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክትም “ትውልድን ለማነጽ በተሰራው ስራ አብራችሁን የሰራችሁትን ሁሉ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እያመሰገንኩ፣ እነዚህ ትምህርት ቤቶች የእናንተ እና የልጆቻችሁ ሀብት በመሆናቸው እንድትንከባከቧቸው አደራ እላለሁ” ብለዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት












