የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለጋዜጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በምክክር ሂደቱ ተሳትፎ ካላደረጉ የፖለቲካ ፖርቲዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቃል አቀባይ ጥበቡ ታደሰ እንደ አገር ከሚንቀሳቀሱ 63 የፖለቲካ ፓርቲዎች ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት በሂደት እየተሳተፉ ቢሆንም ጥቂት የፖለቲካ ፖርቲዎች ተሳትፎ እያደረጉ አለመሆኑ ገልጸዋል።
በምክክር ሂደቱ ተሳትፎ የነበራቸው ግን ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ከሂደቱ ካቋረጡ ከኢሕአፓ፣መኢአድ እና እናት ፓርቲ ጋር ውይይት በማድረግ በቀጣይ ተሳትፎአቸውን ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል።
የፖለቲካ ፖርቲዎቹ ከምክክር ኮሚሽኑ ጋር በነበራቸው የውይይት መድረክ ካስቀመጧቸው ሀሳቦች የእርስበእርስ ጦርነቶችን በድርድር መፍታት፣ፍቃደኛ ያልሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማሳተፍ፣ የፍርድ ሂደታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ፖለቲከኞች፣የሚዲያ ባለሙያዎች ና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተሳትፎ ማሳደግ ይገባል የሚሉ ሀሳቦች መነሳታቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።
በቀጣይም ኮሚሽኑ ያልተሳተፉ የፖሊቲካ ፓርቲዎችን ለማሳተፍ ጥረቱን እንደሚቀጥል አስታውቋል።
እንዲሁም በህግ ጥላ ስር የሚገኙ ዜጎችን በምክክር ሂደቱ ለማሳተፍ የሚረዱ ውይይቶች መደረጋቸው ተመላክቷል።
የትግራይ ክልልን የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መርሃግብርን በምን ሂደት ላይ ይገኛል የሚለውን ጉዳይ ላይ ከጋዜጠኞች የቀረበ ጥያቄ ሲሆን ካሚሽኑም ክልሉን ለማሳትፍ ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል።
ሆኖም እስካሁን በተደረጉ ጥረቶች የተለየ ምላሽ አለመኖሩ ተገልጿል።
በሰላም ይልማ












