የብራይተኑ ሁለገብ አማካኝ ባጋጠመው ጉዳት ለሶስት ወር ከሜዳ እንደሚርቅ እና የቀዶ ህክምና እንደሚደረግለት ታውቋል።
የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በኢፕስዊች ታውን በውሰት ያሳለፈው ኤንሲሶ ክለቡ በቋሚነት ሊሸጠው ቢፈልግም መጎዳቱን ተከትሎ ዝውውሩ ተሰናክሏል። ፓራጓዊው አማካኝ በአሰልጣኝ ፋቢያን ሄርዝለር የቡድን ስብስብ እንደማይፈለግ አስቀድሞ ተነግሮታል ተብሏል።
ተጫዋቹ በደቡብ አሜሪካ የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ላይ በሚገኘው የብራይተን የቡድን ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ህክምናውን ለማድረግ ወደ እንግሊዝ ይመለሳል ተብሏል። የ21 ኤንሲሶ ጉዳት ማስተናገዱ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ወሳኝ ጊዜ ላይ ለሚገኘው የፓራጓይ ብሔራዊ አሳዛኝ ዜና ተብሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












