ከ60 አመታት በላይ በምዕራብ አፍሪቃዊቷ ሀገር ሴኔጋል የነበረው የፈረንሳይ ጦር ሙሉ ለሙሉ ሀገሪቱን ለቆ ወጥቷል፡፡
በሁለቱ የወታደራዊ ካምፖች የነበረው ጦሩ፤ ይህን እርምጃ የወሰደው የሴኔጋል ዜጎች መንግስታቸው ከፈረንሳይ ጋር ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት እንዲያቋርጥ እና የሴኔጋል ሉዓላዊነት እንዲረጋገጥ ባደረጉት ግፊት ነው።
የሁለቱም ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት ስነ-ስርዓት ላይ የፈረንሳይ ጦር ካምፕ ጌሌን እና በዳካር አየር ማረፊያ የሚገኘውን የአየር ማረፊያ ለሴኔጋል ባለስልጣናት አስረክቧል።
በአፍሪካ የፈረንሳይ ኃይሎች ኃላፊ ጄኔራል ፓስካል ኢያኒ እንደገለጹት፤ በምዕራብ እና በመካከለኛው አፍሪካ ውስጥ ወታደራዊ ሰፈሮችን ለቆ መውጣት የፈረንሳይ ውሳኔ ነው፡፡ ከሴኔጋል ቀደም ብሎ ከቡርኪናፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀር ከወጣች በኋላ በምዕራብ አፍሪካ የፈረንሳይ ወታደራዊ ቆይታ ማብቃቱን እንደሚያሳይ ተገልጾል፡፡
የሴኔጋል ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል ምባዬ ሲሴ እንደተናገሩት፤ ይህ ተግባር ዋና ግቡ በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰላም እንዲሰፍን አስተዋጽኦን ማበርከት ነው።
ዘገባው የ አር ቲ ነው
በ ሔርሜላ ተመስገን












