ዛሬ ጁላይ 18 የነጻነት ቀንዲል ፈንጣቂ ኔልሰን ማንዴላን የተወለዱበትን ቀን በማስታወስ ዓለም ዓቀፍ የኔልሰን ማንዴላ ቀን ተብሎ ይጠራል፡፡
ጁላይ 18 1918 የተወለዱት ኔልሰን ሮሊሂሃላ ማንዴላ የሃያኛው ክፍለ ዘመን ከባርነት እንዲላቀቅ ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመንም የተሻለ እንዲሆን የጣሉት የፓንአፍሪካኒዝም አሻራ ታሪክ የሚዘነጋ አይደለም፡፡
በዴሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጠው የመጀመርያው የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ፕሬዝዳንት የነበሩት ማዲባ በጸረ አፓርታይድ ትግል ውስጥ የነበራቸው ሚና ከፍተኛ ሲሆን የሀገሪቱ ዜጎችም የደቡብ አፍሪካ አባት ሲሉም ይጠሯቸዋል፡፡
እንደ አውሮፓውያኑ 1962 ኔልሰን ማንዴላ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ወታደራዊ ሥልጠናን ወስደው እንደነበር የታሪክ መዛግብት ምስክር ናቸው፡፡
የዚህ ዓመት የማንዴላ ቀን መሪ ቃል “ኢ ፍትሐዊነትን እና ድሕነትን ለመታገል ካሰብን መፍትሔው በእጃችን ነው” የሚል ነው፡፡
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












