የኢንትራክት ፍራንክፈርቱ አጥቂ ሆጎ ኤኪቲኬ በያዝነው የዝውውር ገበያ ወደ ኒውካስትል መጓዙ የማይቀር መሆኑን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ኒውካስትል ዩናይትድ ለ23 አመቱ ተጫዋች ለክለቡ ሪኮርድ በሆነ ሂሳብ 80 ሚሊዮን ፓውንድ ያቀረበ ሲሆን፣በጀርመኑ ክለብ ተቀባይነት ማግኘቱ ተመላክቷል። ተጫዋቹ በያዝነው ሳምንት የህክምና ሂደቱን ለማጠናቀቅ ወደ እንግሊዝ ይጓዛልም ተብሏል።
ሁጎ ኤኪቲኬ በተጠናቀቀው የውድድር አመት በቡንደስሊጋው 15 ግቦችን ሲያስቆጥር፣8 ወደ ግብ የተለወጡ ኳሶችን ማቀበል ችሏል። በቀጣይ የውድድር አመት የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ የሆነው ኒውካስትል፣አስደናቂ አቋም ላይ ከሚገኘው አጥቂው አሌክሳንደር ኢሳቅ ላይ ኤኪቲኬንም በማካተት በይበልጥ ራሱን ለማጠናከር ተዘጋጅቷል።
የአሰልጣኝ ኤዲ ሃው ቡድን ከቀናት በፊት ከኖቲንግሃም ፎረስት የመስመር አጥቂውን አንቶኒ ኤላንጋን በ55 ሚሊዮን ፓውንድ የግሉ መድረጉም ይታወሳል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












