ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በምታዘጋጀው 2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።
2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማካሄድ መሰራት ያለባቸው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር እየተመከረ ነው።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን በጳጉሜ 1 እስከ 5 በሚካሄደው ሁለተኛው የአር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አፍሪካውያን ለህልውና አስጊ የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን በመምከር ዘላቂ መፍትሄዎችን ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
በአህጉራዊ ጉባኤ የተሳካ ለማድረግ የፋይናንስ፣የቴክኒክ እና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ከአጋር አካላት ውይይት እየተደረግ ይገኛል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን አፍሪካ ለአየር ንብረት ዝቅተኛ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቅት ቢኖራትም በተጽዕኖው ማምለጥ ባለመቻሏ አማራጭ መፍትሄ ላይ ለመምክር ያግዛል ብለዋል። በፓሪሱ ስምምነት ለአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቅት የሚለቁ ያደጉ አገራት ለታዳጊ አገራት የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ቢቀመጡ አተገባበሩ ዝቅተኛ መሆኑ ይቀመጣል።
ይህን እና መሰል የአየር ንብረት ፋይናንስን ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
በ ሰላም ይልማ












