የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF)፣ ቅዳሜ በሱዳን ሰሜን ኮርዶፋ ግዛት በጀመሩት ጥቃት ወደ 300 የሚጠጉ ሰዎችን መገደላቸው ተገለጸ ።
የሱዳን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን “የድንገተኛ አደጋ ጠበቆች” ባወጣው መግለጫ፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) ቅዳሜ በሰሜን ኮርዶፋን ግዛት በጀመሩት ጥቃት በመቶ የሚቆጠሩ ንጹሃን ለሞት መዳረጋቸውን አስታውቋል ።
በአሁኑ ወቅት በፓራሚሊታሪው ቁጥጥር ስር በምትገኘው ባራ ከተማን ጨምሮ በሌሎች መንደሮች ላይ በፈጸሙት ጥቃት ነው 300 የሚሆኑ ንጹሃን ለሞት ተዳርገዋል የተባለው ።
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች ሻግ አልኖም በሚባል አንድ መንደር በከፈቱት ጥቃት ከ200 በላይ ሰዎች በእሳት እና በጥይት ሲገደሉ፣ በሌሎች መንደሮች ላይ በተፈጸሙ የዝርፊያ ወረራዎች ደግሞ 38 ንፁሃን መሞቻቸውን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኑ በመግለጫው አስታውቋል ።
በተጨማሪም ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ እሁድ ዕለት ሀሚድ በተባለች መንደር ላይ ጥቃት በማድረስ 46 ሰዎችን መግደሉ ቡድኑ በመግለጫው አክሎ አስታውቋል። ነፍሰ ጡር እናቶች እና ህፃናት በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል እንደሚገኙበትም ተገልጿል ።
የRSF ኃይሎች በሲቪል መኖሪያ አካባቢዎች ላይ እያደረሱት ያለው ጥቃት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን ስጋት ውስጥ የከተተ ሲሆን፣ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ቢሮም አሳሳቢ ሆኗል ነው የተባለው ። ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት በቀጠናው በተከፈተው አዲስ ጥቃት በግጭቱ ሳቢያ በሲቪሎች ላይ እየደረሰ ያለውን ከፍተኛ ሰቆቃ በድጋሚ የሚያሳይ ነው ተብሏል።
የኮርዶፋ ቀጠና ከሚያዝያ 2023 ጀምሮ በሱዳን እየተካሄደ ባለው የእርስ በእርስ ጦርነት ቁልፍ ከሆኑ ግንባሮች አንዱ ሲሆን፣ ፈጥኖ ደራሹ ሀይሉ (RSF) በዚህ አካባቢ ከሱዳን ጦር ጋር ሲፋለም ቆይቷል።
ዘገባው የዘጋርዲያን ነው
በ ሰላማዊት ወልደገሪማ












