የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ በክለቦች የዓለም ዋንጫ በፒኤስጂ 4-0 ከተሸነፉ በኋላ ከቪኒሺየስ ጁኒየር እና ከኪሊያን ምባፔ ጋር ውይይት ለማድረግ መዘጋጀቱ ተዘግቧል።
አዲሱ አሰልጣኝ ሁለቱ የፊት መስመር ተጫዋቾች በጨዋታው ላይ የወረደ ተነሳሽነት አሳይተዋል የሚል ቅሬታ አለው። በተለይም ከኳስ ውጭ የነበራቸው እንቅስቃሴ ስፔናዊውን አሰልጣኝ አበሳጭቶታል።
አሎንሶ በቡድኑ ውስጥ የሚታዩ ጉልህ ችግሮችን ለመፍታት መጓጓቱን ማርካ ዘግቧል። የሪያል ማድሪድ አመራሮችም በተጫዋቾች መካከል ያለው አንድነት መላላት እና የቡድን መንፈስ ማሽቆልቆል እንዳሳሰባቸው ዘገባው አስረድቷል።
የክለቡ አስተዳደር ባለፈው የውድድር ዘመን ተጫዋቾቹ እርስ በርሳቸው ያልተገባ ባህሪን ሲያሳዩ ታዝቧል ተብሏል። ቪኒሺየስ ጁኒየር በ2024 የባሎንደ’ኦር ሽልማት ሁለተኛ ሆኖ ካጠናቀቀ በኋላ የአቋም መዋዠቅ እየተስተዋለበት ነው።
በሁሉም ውድድሮች 44 ጎሎችን በማስቆጠር የአውሮፓ የወርቅ ጫማውን ያሸነፈው ኪሊያን ምባፔ በበኩሉ፣ የቡድን ስራ ላይ የበለጠ መስራት እንዳለበት ተነግሮታል።
በ-ይበልጣል ሰውነት












