የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪዬር ስታርመር ከፈረንሳይ ድንበር አቋርጠው ወደ እንግሊዝ የሚገቡ ሕገ ወጥ ስደተኞችን በተመለከተ አዲስ እግድ እና ክልከላ በማስቀመጥ ስምምነት ማድረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የስደተኞችን ጉዳይ በሚመለከት ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት መነጋገራቸው የተጠቀሰ ሲሆን በተጨማሪም የአውሮፓ ሀገራት ጥምረት ወታደራዊ የመከላከል አቅምን በተመለከተ መወያየታቸው ተጠቅሷል፡፡
በተለይም ስደተኞች በጀልባ አድርገው ማቋረጣቸው ትልቅ አደጋ የሚፈጥር በመሆኑ የቁጥጥር ስራው እንደሚጠናከር ነው የተገለጸው፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ ከፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ የገቡ ስደተኞች ቁጥር ከ21 ሺህ በላይ መሻገሩን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












