የ67 አመቱ ጀርማናዊ አሰልጣኝ እግራቸው ላይ በገጠማቸው ድንገተኛ ሕመም ለአስቸኳይ ቀዶ ሕክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ዘ ሰን ዘግቧል።
የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ራኚክ የገጠማቸው ጉዳት የአስከፊነት ደረጃ በውል ያልተለየ ስሆን፣የኦስትሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቃል አቀባይ ቶማስ ቱርኬዝ “በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ”በማለት ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።
ዘ ሰን ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አሰልጣኙ በነገው ዕለት ከሆስፒታል ሊወጡ እና ወደ መኖሪያ ቤታቸው ይገባሉ።
አሰልጣኝ ራልፍ ራኚክ ጤንነታቸው ሲመለስ የመጀመሪያ ስራቸው የሚሆነው ለ2026 አለም ዋንጫ ለማለፍ ወሳኝ ጊዜ ላይ የሚገኘውን የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን ከሳይፕረስ እና ቦስኒያ ሄርዞጎቪኒያ ለሚያደርገው ጨዋታ ማዘጋጀት ይሆናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












