የሰሜን ለንደኑ አርሰናል በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሁለተኛ የአማካኝ መስመር ተጫዋች የግሉ አድርጓል።
መድፈኞቹ ዴንማርካዊውን ተጫዋች ከብሬንትፎርድ ለመውሰድ 10 ሚሊዮን ፓውንድ የመነሻ ክፍያ መፈጸማቸው ታውቋል። የ31 አመቱ ኖርጋርድ የቶማስ ፓርቴ ተተኪ በመሆን የመጣ ሲሆን፣ለአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታን የቡድን ስብስብ ጥልቀት ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።
ኖርጋርድ ከፊርማ ስነስርዓቱ በኋላ በሰጠው አስተያየት “ቻምፒዮንስ ሊግ የመጫወት ህልሜን ለማሳካት በመቻሌ ደስተኛ ነኝ’’ ብሏል። አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታም”የዳበረ የፕሪምየር ሊግ ልምድ ያለው፣ውስብስብ ታክቲኮችን የሚገነዘብ ተጫዋች በማግኘታችን ተደስተናል” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
ክሪስቲያን ኖርጋርድ ባለፉት ሶስት አመታት የተጋጣሚ ቡድኖችን ማጥቃት በማጨናገፍ ሪከርድ ያስመዘገበ፣የአየር ላይ ኳስ በሚገባ የሚጠቀም እና አደገኛ ኳሶችንም ለአጥቂ መስመር ተጫዋቾች በማድረስም ይደነቃል።
ሁለገቡ አማካኝ በአርሰነል ማለያ 16 ቁጥር የሚለብስ ይሆናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












