Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ሁለተኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ በጳጉሜን ወር ይካሄዳል – አምባሳደር ነብያት ጌታቸው

ሁለተኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ በጳጉሜን ወር ይካሄዳል - አምባሳደር ነብያት ጌታቸው

July 10, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

ከ25 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚታደሙበት ሁለተኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ እና ሁለተኛው የተመድ የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ በጷጉሜን ወር እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ የሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው፣ የሚኒስቴሩን የበጀት ዓመት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ በወቅታዊ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

‎አምባሳደሩ ከፖለቲካ ዲፕሎማሲ ሥራዎች መካከል ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በማጠናከር፣ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባዎችን በማከናወን እና ሌሎችንም ሀገራዊና ቀጠናዊ ትስስር የሚያጠናክሩ ዲፕሎማሲያዊ ተግባራትን ማከናወን መቻሏን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ከህዳሴው ግድብ ጋር ተያይዞ የግብጽን አመፅ ቀስቃሽነት ለማስቆምና ድርድሩ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ሳይሆን በአፍሪካ ህብረት እንዲታይ ሆኗል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር ለ968 የተለያዩ ሀገራት ዜጎች የትምህርት ዕድል መስጠቷንም ተናግረዋል። እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት ጋር የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብሩ 11 ስምምነቶች ተፈርመው በፓርላማ መፅደቃቸው አውስተዋል።

‎ጎረቤት ሀገራትን ባስቀደመ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲና መርህ ጥላ ስር የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ትብብሮችን ለማጠናከር በትኩረት መሰራቱንም አምባሳደር ነብያት ጠቅሰዋል።

‎አምባሳደር ነብያት ከኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ አንጻር በሰጡት ማብራሪያ፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄና በቅርቡ ተግባራዊ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ድጋፍ እንዲያገኝ ሰፋፊ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረው፣ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗ ተቀባይነትና ተደማጭነቷ ከፍ እንዲል ማድረጉን አውስተዋል።

‎የተለያዩ መድረኮችን በመጠቀም የኢትዮጵያን ምርቶች፣ የቱሪዝም መዳረሻዎችን እና ሌሎች መሰል ኢኮኖሚያዊ አቅሞችን የማስታወቅ ስራ የተከናወነ ሲሆን፤ በዚህም 806 ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የቅድመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት ማከናወናቸውን ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ በ21 ሀገራት በችግር ውስጥ የነበሩ ከ131 ሺህ በላይ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ነው ያሉት።

‎የዜጎችን ደህንነትና ክብር የማስጠበቅ ስራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቀዳሚ ኃላፊነት ነው ያሉት ቃል አቀባዩ፤ በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ 1 ሺህ 556 ዜጎች መብታቸው እንዲከበር ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል ሲል የዘገበው ኢ ፕ ድ ነው፡፡

Source: @NBCEthiopia
Via: NBCEthiopia
Tags: EthiopiaFacebookMeta
ShareTweetShare
Previous Post

የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ራልፍ ራኚክ በሕመም ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ

Next Post

ኢንተርኔት የማይፈልገው አዲሱ መተግበሪያ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ኢንተርኔት የማይፈልገው አዲሱ መተግበሪያ

ኢንተርኔት የማይፈልገው አዲሱ መተግበሪያ

ክሪስቲያን ኖርጋርድ በይፋ አርሰናልን ተቀላቀለ

ክሪስቲያን ኖርጋርድ በይፋ አርሰናልን ተቀላቀለ

በቀይ ባሕር አንድ መርከብ ስትሰጥም የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል መውጣቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

በቀይ ባሕር አንድ መርከብ ስትሰጥም የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል መውጣቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?