ዶናልድ ትራምፕ የላይቤሪያውን ፕሬዚዳንት “እንግሊዘኛውን የት ተማሩት?” ሲሉ በግርምት መጠየዋቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
የተለያዩ የአፍሪካ መሪዎችን በዋይት ሀውስ እያስተናገዱ ባሉበት ሰዓት መሪዎቹ በተለያየ ቋንቋ ሲናገሩ አድምጠዋል ዶናልድ ትራምፕ፡፡ የላይቤሪያው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦአካይ ወደ መነጋገሪያው ብቅ ሲሉ በአስደናቂ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቃት ተናግረዋል።
ለዚህም ነው የላይቤሪያ ይፋዊ ቋንቋ እንግሊዘኛ መሆኑን የዘነጉት ትራምፕ “እንዲያው ከዬት አመጡት?”የሚል ከዲፕሎማሲ ይልቅ ቋንቋ ላይ ያተኮረ ጥያቄ ያነሱላቸው ለላይቤሪያው ፕሬዚዳንት፡፡ ቦአካይ “ላይቤሪያ የረዥም ጊዜ የአሜሪካ ወዳጅ ናት እናም በእናንተ ታላቋን አሜሪካ ዳግም ማምጣት ፖሊሲም እናምናለን ”ብለዋቸዋል ለትራምፕ።
ከዲፕሎማሲው በላይ እጅጉን በቋንቋ ችሎታቸው የተማረኩት ሪፐብሊካኑ ትራምፕ “የሚገርም እንግሊዘኛ ፡፡” “ከዬት አመጡት ይህን የመሰለ ያማረ ቋንቋ?” በሚል አድንቀዋቸዋል። ትራምፕ ሲቀጥሉ “በውኑ ላይቤሪያ ነው የተማሩት ?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ቦአካይም . “አዎ ክቡርነቱ” በሚል መልሰዋላቸዋል። ትራምፕ በዚህ መድረክ እና ጠረጴዛ ላይ በርካቶችን አይቻለሁ ለርሶ የቀረበ ንግግር ያደረገ እንኳን አይቼ አላውቅም በሚልተደንቀውባቸዋል፡፡ ላይቤሪያ በፈረንጆቹ 1822 በነጻ ጥቁር አሜሪካውያን በቅኝ ግዛት ግንዛቤ ውስጥ መመስረቷ ይታወሳል፡፡
ምንም እንኳን በላይቤሪያ በርካራ ነባር ቋንቋዎች ቢነገሩም እንግሊዘኛ ብሄራዊ መግባቢያቸው ሆኗል።
በ-ቢኒያም ካሴ












