የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ነገ የሚያከበረውን 90ኛ የምስረታ በዓል አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የማህበሩ ፕሬዚደንት አበራ ቶላ፤ ማህበሩ ወደ 12 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሀብት እንዳለው፣ እንዲሁም በሀገሪቱ ያሉት ሀብቶች ገቢ እንዲያመነጩ በማድረግ ከውጭ የሚያገኘውን እርዳታ 80 በመቶ ለመቀነስ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ማህበሩ ያሉትን ህንፃዎች አከራይቶ ገቢ በማመንጨት፤ የእርሻ መሬቶችን በማምረት፤ የአባላትን ቁጥር በማሳደግ ከውጭ የሚያገኘውን እርዳታ ለመቀነስ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ማህበሩ 30 በመቶ የራሱ የገቢ ምንጭ አለው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ በቀጣይ ጥቂት ዓመታት ራሱን ችሎ እንዲቆም ለማድረግ ሰፊ ስራ እየተሰራ ነው ሲሉ ገለጸዋል።
ማህበሩ የተፈጥሮና የሰው ሰራሽ ችግሮች በተከሰቱባቸው አካባቢዎች የሰባዓዊ እርዳታ ድጋፍ ከማድረስ በተጨማሪ ተቋማትን የማቋቋም ስራ እየሰራ ነው መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ማህበሩ የተጎዱትን የሚያፅናና፣ የተሰበሩትን የሚያቃና፣ የወደቁትን የሚያነሳ እንዲሁም በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ፈጣንና ቀልጣፍ የሰበአዊ ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጥ ለማድረግ እየተስራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ማህበሩ 90 ዓመቱን የሚያከብርበት አላማ ድጋፍ ላደረጉ ተቋማትንና በጎ ፍቃደኞችን ለማመስገንና እውቅና ለመስጠት እንደሆነ ጠቅሰው፤ ማህበሩ ላለፉት 90 ዓመታት የሰራቸው ስራዎች በምስል እንደሚታይ አብራርተዋል ሲል የዘገበው ኢፕድ ነው።












