። ። ። ። ። ። ። ። ። ።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በኋይት ሃውስ ሊገናኙ እንደሆነ ተገለጸ፡፡
የአሜሪካ ባለሥልጣናት ትራምፕ እና ኔታንያሁ ከስድስት ቀናት በኋላ በኋይት ሃውስ እንደሚገናኙ ይፋ አድርገዋል፡፡
በእስራኤል ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ጉዳይ ዋነኛው አጀንዳ መሆኑ ሲገለጽ፣ የቀሩ ታጋቾችን በመለቀቃቸው ዙርያ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ ሮን ዴርመር በዚህ ሳምንት በዋሽንግተን መኖራቸውን እና በቀጣይ ሳምንት ሰኞ ዕለት ደግሞ ትራምፕ እና ኔታንያሁ በአካል ተገናኝተው ከጋዛው ጉዳይ ባለፈ ስለ ኢራን እና ሶሪያ ጉዳይ እንደሚነጋገሩ ነው የተጠቀሰው፡፡
ትራምፕ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው እስራኤል ስምምነት ታድርግ፤ ታጋቾችም ይለቀቁ ብለው ከጻፉ በኋላ እስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ ክፍል ከፍተኛ የቦምብ ጥቃት አድርሳ የበርካቶች ሕይወት ማለፉ የሚዘነጋ አይደለም ሲል ኤዢያ ዋን ዘግቧል፡፡
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ












