የ2024/25 የስራ አፈጻጸሙን አስመልክቶ መግለጫ የሰጠው አዋሽ ባንክ ከ22 ቢሊዮን በላይ ብር ማትረፉን አስታወቀ።
መግለጫውን የሰጡት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሃይ ሽፈራው እንደገለጹት፤ ባንኩ 52 አዳዲስ ቅርንጫፎችን መክፈቱን እና አጠቃላይ የቅርጫፎቹን ቁጥር ከ989 በላይ ማድረስ ስለመቻሉም ገልፀዋል፡፡
አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር ከ15 ሚሊዮን በላይ ማድረሱም ተነስቶ፣ አንድ ትሪሊዮን የሚጠጋ ብርም በዲጂታል መልኩ መዘዋወሩን አመላክተዋል፡፡ አሁን ላይ የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ 106 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ42 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ተገልጿል።
ከወለድ ነጻ የሆነ የባንክ አገልግሎት ተቀማጭ ገንዘብም 37 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መሆኑንም ተመላክቷል፡፡ ባንኩ በዓመቱ መጨረሻ ከታክስ በፊት 22 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ማትረፉንም ገልጿል። በዚህ ዓመት ብቻ 7 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የካፒታል እድገት መመዝገቡም ነው የተጠቆመው።
በሚቀጥሉት ዓመታትም የያዘውን የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በስፋት እንደሚሳተፍ እና የጀመራቸውን ስራዎች በስፋት እንደሚከወንም ባንኩ በመግለጫው አመላክቷል፡፡
በ ማህሌት ግርማ












