የዓለም ስፖርት ጋዜጠኞች ቀን በዛሬው እለት “የስፖርት ጋዜጠኞች ስፖርትን ለማስተዋወቅ የሚያገለግሉትን አገልግሎት ለማክበር” በሚል መሪ ቃል በዓለምአቀፍ ደረጃ ተከብሮ ይውላል።
እ∙ኤ∙አ በ1924 በፓሪስ በተካሄደው ኦሊምፒክ የተቋቋመ ሲሆን ይህም የስፖርት ጋዜጠኞችን ለመደገፍ እና የፕሬስ ነፃነትን በስፖርት ዘርፍ ለማረጋገጥ ያለመ ነበር። በዚህም ጁላይ 2 “የዓለምአቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች ቀን” ተብሎ ተወስኗል።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጁላይ 2 የስፖርት ጋዜጠኞች የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚናን በማሳየት ከአድልዎ የጸዳ፣ በስነምግባር የታነፀ ስፖርታዊ ዘገባዎችን ማቅረብ እንደሚያስፈልግ በማበረታት እየተከበረ ቀጥሎል፡፡
በ-ሄርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












