የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ እና ሊቃነ ጳጳሳት የተሳተፉበት የችግኝ መትከል መርሃ ግብር አከናውነዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት የተጀመረው “በመትከል ማንሰራራት” የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር 7.5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ ተይዟል። በቀጣይ ክረምት ወራትም አረንጓዴ አሻራን ጨምሮ በሌሎችም የከተማችን ልማቶች የሚያደርጉትን ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሃይማኖት አባቶች ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ሰኔ 22 / 2017 ዓ/ም ያስጀመሩት የዘንድሮው የከተማችን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማንሳታቸው የሚታወስ ነው።
በችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ ላይ ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ማትያስን ጨምሮ ሌሎች ብጹዓን አባቶች፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎችም በየደረጃው የሚገኙ የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ነው።












