የ40 ዓመቱ አሜሪካዊ በአልቲሜት ፋይቲንግ ሻምፒዮና የአጭር ጊዜ ቆይታ ካደረገ በኋላ ከድብልቅ ማርሻል አርት በ2019 ነበር ጡረታ የወጣው።
አስክረን ካጋጠመው የሳምባ ምች ህመም ያገግም ዘንድ የልገሳ ተማጽኖውን ዩቱበርና ቦክሰኛው ጄክ ፖል ሲያስተባብር ቆይቷል። ፖል በ2021 በቦክስ ግጥሚያ አስክረንን አሸንፏል። ከእርሱ ትውልድ ምርጥ አሜሪካዊ ተፋላሚዎች እንደ አንዱ የሚቆጠረው አስክረን በቤላተር እና ዋን ሻምፒዮና የዌልተር ሚዛን ሻምፒዮን ነበር።
ወደ ድብልቅ ማርሻል አርት ከመግባቱ በፊት የሁለት ጊዜ ብሄራዊ ሻምፒዮን እና የ2008 የአሜሪካ ኦሊምፒክ ቡድን አባል ነበር። በ2019 ለድብልቅ ማርሻል አርት አወዳዳሪው አልቲሜት ፋይቲንግ ሻምፒዩና (UFC) ከፈረመ በኋላ በመጀመሪያ 20 ፍልሚያዎች አልተሸነፈም።
በ22 ፍልሚያዎች 19 በማሸነፍ ከድብልቅ ማርሻል አርት ጡረታ ወጥቷል። ሶስት ልጆች ያሉት አስክረን በዊስኮንሲን የራሱን የፍልሚያ አካዳሚ ከፍቷል።
በ ይበልጣል ሰውነት
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












