በርካታ የአውሮፓ ከተሞች በከባድ ሙቀት እየነደዱ ሲሆን፣ ቱርክ ደግሞ በሰደድ እሳት እየተለበለበች ነው።
ቱርክ በከባድ የሰደድ እሳት እየታመሰች ሲሆን፣ 50 ሺ የሚሆኑ የምዕራብ ቱርክ ነዋሪዎች አካባቢን እንዲለቁ ተድርጓል። እሳቱ በፍጥነት በመዛመቱ በርካታ አካባቢዎችን በማውደሙ እየተዘገብ ይገኛል።
በአንጻሩ በፈረንሳይና በእንግሊዝ ከፍተኛ ሙቀት መመዝግቡ ተሰምቷል። በእንግሊዝ ከዚህ ቀደም ከነበረ እጅጉን የላቀ የሙቀት መጠን ተከስቷል ነው የተባለው። በጣሊያን ሁለት ሰዎች በሙቀቱ የተነሳ ህይወታቸው ሲቀጠፍ፣ በያዝነው ሳምንት በሀገሪቱ የተመዘገበው የሙቀት መጠን 45 ዲግሪ ሴሊሺየስ ነው የተነገረው።
በእንግሊዝ ከተሞች ደግም ከ33.5 – 35 ዲግሪ ሴሊሺየስ ደርሷል። ይሄ የአየር ጠባይ እንግሊዝ አይታው የማታውቀው አይነት ከፍተኛው የሙቀት መጠን ነው ተብሏል። የአየር ንብረት ትንበያዎች እንደሚጠቁሙት የሙቀት መጠኑ ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ያስነበብው ቢቢሲ ነው።
ዳዊት ዓለሙ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












