የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ሃገራቸው የኢራንን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ ለመግደል ትፈልግ ነበር።
ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት በኢራን እና እስራኤል መካከል በቅርቡ በተካሄደው የ12 ቀናት ጦርነት እና በተኩስ አቁም ስምምነት ከተጠናቀቀ በኋላ ነው፡፡ ካትዝ እንደገለጹት ሃገራቸው ኻሚኒን ለመግደል ከአሜሪካ ፈቃድ እንደማያስፈልጋት ጠቅሰው፣ ዋሽንግተን ግድያውን ውድቅ አድርጋለች የሚለውን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባ አስተባብለዋል።
ኻሚኒ በቅርቡ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ያሉ ቢሆንም ከኢራን ጄኔራሎች ጋር ያላችዉን ግንኙነት የሚያሳይ ምንም ዓይነት መረጃወች ግን አልወጡም ነው የተባለው። ኻሚኒን መግደል በግጭቱ ውስጥ ትልቅ መባባስን ሊያመጣ እንደሚችልም እየተገለጸ ነው።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጦርነቱ ዋና አላማ የአገዛዝ ለውጥ ማምጣት እንደሆነ በተለያዩ ጊዜያት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
በ ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












