በአሜሪካ አስተናጋጅነት እየተስተናገደ የሚገኘው እና 32 ክለቦችን ያሳተፈው ውድድሩ የምድብ ጨዋታዎች ተደርገው ተጠናቀዋል።
በ16 ክለቦች መካከል የሚደረገው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከነገ ጀምሮ መካሄዱን ይቀጥላል። በመድረኩ የአሸነፊነት ቅድመ ግምት የተሰጠው ፒኤስጂ ከአሜሪካው ክለብ ኢንተር ሚያሚ የተገናኙበት እና ሪያል ማድሪድን ከ ጁቬንቱን ያፋጠው ግጥሚያ ተጠባቂ ሆኗል።
ፒኤስጂ ከቀድሞ ተጫዋቹ ሊዮኔል ሜሲ ቡድን ጋር በእለተ ዕሁድ የሚገናኝ ሲሆን፣ከአውሮፓ ክለቦች ውጪ ዋንጫውን ሊያሳካ ይችላል የተባለው ኢንተር ሚያሚ ፈተና ሊደቅንበት እንደሚችል ተገምቷል።
ጁቬንቱስ ከምድብ ሰባት አንደኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ ያደረገው ትግል በማንችስተር ሲቲ በመሸነፉ ምክንያት ስላልተሳካላት ከምድቡ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ሪያል ማድሪድን ለመግጠም ተገዷል። የአሰልጣኝ ዣቪ አሎንሶ ማድሪድ ምድቡን በበላይነት ቢያጠናቅቅም፣በተጋጣሚ ቡድኖች ሲፈተን በተደጋጋሚ ታይቷል። ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን የዋንጫው አሸናፊነት ግምት ከሚሰጣቸው ቡድኖች ውስጥ ሎስ ብላንኮዎቹም ይገኙበታል።
በሌሎች የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ኢንተር ሚላን ከፍሉሚኔንሴ፣ማንችስተር ሲቲ ከአል ሂላል፣ ቦሩሲያ ዶርትሞንድ ከ ሞንቴሪ፣ፍላሚንጎ ከባየርን ሙኒክ፣ቤኔፊካ ከቼልሲ እና ፓልሜራስ ከ ቦታፎጎ የሚጫወቱ ይሆናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












