የግራ መስመር ተከላካዩ ሚሎስ ኬርኪዝ ከቦርንመዝ ወደ ሊቨርፑል ያደረገውን ዝውውር ክለቡ ይፋ አድርጓል።
ሊቨርፑል ለ21 አመቱ ተጫዋች 40 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ያደረገ ሲሆን፣የአምስት አመት ውል አስፈርሞታል። ኬርኬዝ በተጠናቀቀው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የውድድር አመት በአንዶኒ ኢራኦላ ቡድን ድንቅ አቋም ካሳዩ ተጫዋቾ መካከል አንዱ ነው።
ለቦርንመዝ በሁሉም የውድድር አመቱ ጨዋታዎች የተጫወተ ሲሆን፣ሶስት ግቦችን አስቆጥሮ፣አምስት ወደ ግብ የተለወጡ ኳሶችን ደግሞ ለቡድን ጓደኞቹ አቀብሏል። አሰልጣኝ አርን ስሎት የመስመር ተከላካይ ቦታ ላይ ከፍተኛ ለውጥ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
አስቀድመው በቀኝ መስመር ተከላካይነት የአሌክሳንደር አርኖልድ ተተኪ እንዲሆን ጄረሚ ፍሪምፖንግን ከባየር ሊቨርሱሰን ማምታቸው ይታወሳል። በግራ መስመር ላይም ኤንዲ ሮበርትሰን የአቋም መቀነስ እና በክለቡም የሚኖረው ዘለቄታ አለመታወቁ ኬርኬዝን እንዲያስመጡ አስገድዷቸዋል።
ሊቨርፑል በተያዘው የዝውውር ገበያ ሶስተኛ ተጫዋች ወደ ቡድን ስብስቡ ቀላቅሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












