በመዝጊያው ዕለት ዛሬ በተደረጉ የእግር ኳስ የፍጻሜ ጨዋታዎች አስተናጋጁ ኦሮሚያ ክልል በሁለቱም ጾታዎች አሸናፊ ሆኗል።
ጠዋት 4:00 በጅማ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ኦሮሚያን ከ ደቡብ ኢትዮጵያ ያገናኘው የሴቶች የፍጻሜ ጨዋታ በኦሮሚያ 1-0 ድል አድራጊነት ተጠናቋል። በወንዶች ፍጻሜ በተመሳሳይ ሁለቱ ክልሎች ለፍጻሜ ቀርበው ኦሮሚያ ከመመራት ተነስቶ 2-1 አሸንፏል።
ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በመጀመሪያ አጋማሽ ቀድሞ ጎል ቢያስቆጥርም በሁለተኛው አጋማሽ በተቆጠሩበት ሁለት ጎሎች ነጥቡን አስጠብቆ መውጣት ሳይችል ቀርቷል። የነሀስ ሜዳሊያውን ሲዳማ ክልል አሸንፏል።
በአጠቃላይ የሜዳሊያ የደረጃ ሰንጠረዡ ኦሮሚያ፡ አዲስ አበባ እና አማራ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ውድድራቸውን አጠናቀዋል። ኦሮሚያ ክልል በ90 ወርቅ 81 ብርና 55 ነሀስ ከአናት ተቀምጧል።
አዲስ አበባ በ84 ወርቅ 67 ብር 70 ነሀስ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። አማራ ክልል በ46 ወርቅ 46 ብርና 51 ነሀስ 3ኛ ሆኖ ውድድሩን ጨርሷል።
በ-ይበልጣል ሰውነት












