የኢራን ከፍተኛ መንፈሳዊ መሪ የአያቶላህ አሊ ኻሚኒ ጥቃቱ ካበቃ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የቪዲዮ መልእክት አስተላለፉ።
አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት ሲሆን፣ “በእስራኤል ላይ ድል አድርገናል” እንዲሁም “አቅማችንን ለአሜሪካ ማሳየት ችለናል” በማለት ገልጸዋል።
በቪዲዮው መግለጫም ዩናይትድ ስቴትስ የኢራንን የኒውክሌር መሥሪያ ቤቶችን በማጥቃት “ምንም ጠቃሚ ነገር ማሳካት አልቻለችም” በማለት የገለጹ ሲሆን፣ ዶናልድ ትራምፕ ስለተፈጠረው ነገር “ያልተለመደ እና የተጋነነ” ገለጻ አድርገዋል በማለት ገልጸዋቸዋል።
ከሁለት ሳምንታት በፊት የተጀመረው ይህ ጦርነት መላው ዓለምን አስግቶ ነበር። በእስራኤል እና በኢራን መካከል በርካታ መጠቃቃቶች ተካሒደው ነበር። ኢራን በኳታር የሚገኘውን የአሜሪካን ጦር ሰፈር ከመምታቷ በፊት ዩናይትድ ስቴትስ የኢራንን የኒውክሌር ቦታዎች ላይ ጥቃት አድርሳ እንደነበር ይታወቃል።
በ ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












