Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አሜሪካ የቢዝነስ ጉባኤ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲዋን ማጠናከር የሚያስችል ውጤታማ ተሳትፎ አድርጋለች

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አሜሪካ የቢዝነስ ጉባኤ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲዋን ማጠናከር የሚያስችል ውጤታማ ተሳትፎ አድርጋለች

June 26, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

በአንጎላ አዘጋጅነት በተካሄደው የአፍሪካ አሜሪካ የቢዝነስ ጉባኤ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲዋን የሚያጠናክር ውጤታማ ተሳትፎ ማድረጓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

ጉባኤው ኢትዮጵያ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ጋር የተሰናሰነውን የቢዝነስ ዲፕሎማሲዋን ያጠናከረችበት መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዘርይሁን አበበ ገልጸዋል። በጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይቶች ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ከአንጎላው ፕሬዝዳንትና ከወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ-መንበር ጆ ሌሬንሶ፤ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቦሎስና የአፍሪካ ኮርፖሬት ካውንስል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሎሪ ሊዘር ጋር መወያየታቸውንም ጠቅሰዋል።

ከዋናው ጉባኤ ጎን ለጎን በነበሩ የተለያዩ መድረኮች ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴን ጨምሮ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ(ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር) በኩል ተሳትፎ በማድረግ የኢትዮጵያን አቋም ማንጸባረቅ ተችሏል ብለዋል።

በዚህም በተለይም ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ መሆኗን ያሳየችባቸው፣ የዘርፉን የፖሊሲ ማዕቀፍ ያስተዋወቀችበት፣ የአፍሪካና የአሜሪካ የቢዝነስ ትስስር ምን መምሰል እንዳለበት እይታዋን ያካፈለችባቸው መድረኮች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ትብብር መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ሥምምነትም ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ የጀመረቻቸውን ሰፋፊ ጥረቶች ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን አብራርተዋል።

ሥምምነቱ ከሁለት መቶ ሚሊየን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት ካፒታል የያዘ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ኢትዮጵያ የቱርዝም መሰረተ ልማት በማስፋፋትና መዳረሻ ቦታዎችን በማልማት ምቹ ለማድረግ የያዘችውን ውጥን የሚያግዝ መሆኑን አስረድተዋል።

በተጓዳኝም፤ በጉባኤው የተለያዩ የግንኙነት መረቦች መዘርጋታቸውንም አምባሳደሩ ጨምረው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ልዑክ በዚህ ጉባኤ ላይ መሳተፉ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር በማሰናሰን ኢትዮጵያ ለቢዝነስ ዲፕሎማሲ የሰጠችውን ትኩረት የሚያሳይ መሆኑንም ገልጸዋል።

አምባሳደሩ አክለውም ጉባኤው የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጥረቶች ለማጠናከር ዕድል የፈጠረ መሆኑን ጠቅሰዋል። ጉባኤው በዋናነት ለኢትዮጵያ ምርቶች ገበያ ለማፈላለግ፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል ለማስፋትና፣ የኢንቨስትመንት መዳረሻዎችን በማፈላለግ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልጸዋል።

የዘንድሮው የአፍሪካ-አሜሪካ የቢዝነስ ጉባኤ አሜሪካ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአስተዳደር ዘመን አፍሪካን በተመለከተ የምትከተለው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ድጋፍን መሰረት ካደረገው ወደ ቢዝነስ ዲፕሎማሲ እንዲሸጋገር የተወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ መካሄዱ ልዩ አድርጎታል። ኢትዮጵያ 10ኛውን የአፍሪካ-አሜሪካ ጉባኤ ማዘጋጀቷ ይታወሳል። 17ኛው የአፍሪካ አሜሪካ የቢዝነስ ጉባኤ በትናንትናው ዕለት ተጠናቋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው::

Source: @NBCEthiopia
Via: NBCEthiopia
Tags: AfricaEthiopiaFacebookMeta
ShareTweetShare
Previous Post

“ኔታንያሁ ታላቅ ጀግና ነው” ትራምፕ

Next Post

ላለፉት 10 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ስድስተኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ በኦሮሚያ ክልል የበላይነት ተጠናቋል።

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ላለፉት 10 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ስድስተኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ በኦሮሚያ ክልል የበላይነት ተጠናቋል።

ላለፉት 10 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ስድስተኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ በኦሮሚያ ክልል የበላይነት ተጠናቋል።

የአያቶላህ አሊ ኻሚኒ መልዕክት

የአያቶላህ አሊ ኻሚኒ መልዕክት

ሊቨርፑል የሚሎስ ኬርኬዝን ዝውውር አጠናቀቀ

ሊቨርፑል የሚሎስ ኬርኬዝን ዝውውር አጠናቀቀ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?