በሰሜን አትላንቲክ የጦር ጥምረት ጉባዔ የጋራ መግለጫ ላይ ዩክሬን ትኩረት አልተሰጣትም ተባለ።
በኔቶ የጋራ መግለጫ ላይ ዪክሬን ሁለት ጊዜ ብቻ መጠቀሷ እንደቀደመው ጊዜ ቁልፍ የመወያያ አጀንዳ አለመሆኗን የሚጠቁም ሆኗል ። በኒዘርላንድስ ዘ ሄግ የተደረገው ጉባዔ የጥምረቱን ወታደራዊ በጀት ከማሳደግ አንጻር ትኩረቱን እንዳደረገ ተወስቷል።
በአባል አገራቱ መካከል ያለውን የመከላከያ ትብብር ስለማጠናከርም በሰፊው ጉባዔው መክሯል። ባለ32 ዓባላቱ ኔቶ እያንዳንዱ አገር ከሚያስመዝውግበው ጥቅል አገራዊ ምርት ዕድገት 5 በመቶውን በ2035 ለመከላለያው ለመመደብ ተስማምቷል፡፡
ኔቶ ከሩሲያ የተጋረጠበትን የዩሮ – አትላንቲክ የጸጥታ ስጋት ለመመከት ያለመ ውጥን ነው፡፡ ሞስኮ በተደጋጋሚ ከኔቶ ዓባላት ጋር ጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎቱ እንዳሌላት ብታስረዳም ጥምረቱ ግን ከሶስት እስከ አምስት ዓመታት ጥቃት ይሰነዘርብኛል የሚል ስጋት አለበት፡፡
የሰሜን አትላንቲክ የጦር ጥምረት በ1949 በ12 አገራት ሲመሰረት አንደኛው እና ቁልፉ ዓላማው የዛኔዋን ሶቭዬት ባለችበት ማስቀረት እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።
ዘገባው የአር ቲ ነው።
በ-ቢኒያም ካሴ












