። ። ። ። ። ። ። ። ። ።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ አውሮፓ ህብረት የሰሜን አትላንቲክ የጦር ጥምረት (ኔቶ) የተራዘመ ክፍል እየሆነ መጥቷል አለ፡፡
የኢኮኖሚ ጥምረቱ አደገኛ በሆነ መንገድ ወደ ወታደራዊ ስብስብ ተለውጧል ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌይ ላቭሮቭ።
አውሮፓ ህብረት ከጅምሩ ሲቋቋም ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ታሳቢ አድርጎ የነዋሪውን ህይወት ለማቅለል ነበር ሲሉ በአንድ የሞስኮ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ አስታውሰዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ግን የኔቶ አንድ ቅርንጫፍ እየሆነ መቷል በሚል ሰርጌ ላቭሮቭ ወቅሰዋል፡፡
በአውሮፓ ህብረት እና በኔቶ መካከል የተፈረመው ስምምነት ይህኑ የሚያረጋግጥ እንደሆነም አስታውቀዋል ላቭሮቭ፡፡
የትኛውም የአውሮፓ ህብረት ዓባል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ግዛቱን ለኔቶ ጦር መግቢያ እና መውጫ እንዲፈቅድ ተደርጓል፡፡
ይህ ደግሞ የአውሮፓ ህብረት አገራት ሩሲያን ለመውረር ቀጥተኛ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን ያሳያል በሚል ፈርጀውታል፡፡
ከኔቶ ዋና ጸሐፊ ማርክ ሩቴ በኩል የሚሰጡ አስተያየቶችም ይህኑ የሚያረጋግጡ ሆነውባታል፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












